ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ25ኛ እስከ 28ኛ ሳምንት የውድድር መርሐ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 4/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ25ኛ እስከ 28ኛ ሳምንት ከመጋቢት 25 እስከ ሚያዚያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ።

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከምድረ ገነት ሽሬ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል

አክሲዮን ማህበሩ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ መልስ የሚደረጉ የሊጉ ጨዋታዎችን ይፋ አድርጓል።

ከ25ኛ እስከ 28ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እና አዲስ አበባ ስታዲየም ከመጋቢት 25 እስከ ሚያዚያ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።


 

የ24ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጋቢት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ይደረጋሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር በሚያደርገው የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ምክንያት ሊጉ ለ18 ቀናት ይቋረጣል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም