ቀጥታ፡

የክልሉ አመራር የህዝብን ችግር ቅድሚያ ሰጥቶ መፍታት ላይ ማተኮር አለበት

ሰቆጣ፤ መጋቢት 2/2018(ኢዜአ)፦ በየደረጃው ያለው የክልሉ አመራር የህዝብን ችግር ቅድሚያ ሰጥቶ መፍታት ላይ ማተኮር እንዳለበት የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን(ዶ/ር) አስገነዘቡ።

የሃይማኖት ተቋማት ለክልሉ እድገት የሚተጉ ዜጎችን የማፍራት ኃላፊነታቸውን ማጠናከር አለባቸው

የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሰቆጣ ከተማ በልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ ተካሂዷል።


 

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ እንደገለጹት፤ በየደረጃው ያለው አመራር የህዝብን ችግር ቅድሚያ ሰጥቶ መፍታት ላይ ማተኮር ይገበዋል ብለዋል።

በተለይም በውጤታማነት እና በብቃት የሚመራና የተደራጀ ተቋም በመፍጠር ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለውና ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ አመልክተዋል።

ይህም የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ልማት በማፋጠን የህዝቡን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ጠቁመው ህዝብን ከህዝብ የሚነጥሉ አጀንዳዎችን መመከት እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።


 

በማያያዝም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና አሳታፊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልፀው በየደረጃው ያሉ አስፈፃሚዎችም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አስገንዝበዋል።

የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ ሹመት ጥላሁን በበኩላቸው፤ በአስተዳደሩ ሰላምን በማፅናት የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።


 

በሰቆጣ ከተማ በተካሄደው የውይይት መድረክ የክልልና የብሔረሰብ አስተዳደሩ አመራር አባላት ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም