ቀጥታ፡

በከተማ ግብርና የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት በምርት አቅርቦት ላይ ተጨባጭ ለውጥ እያመጡ ነው  

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦በከተማ ግብርና ዘርፍ የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት በምርት አቅርቦት ላይ ተጨባጭ ለውጥ እያመጡ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ ገለጹ።

በኦሮሚያ ክልል የእንስሳት ሀብት ልማትን ለማዘመን የተቀረፁ ኢንሼቲቮች ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገቡ ነው

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለ975 አንቀሳቃሾች  ዶሮ፣ የዶሮ ኬጅ እና የመኖ ድጋፍ ተደረጓል።


 

‎‎የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ እንደገለጹት፤ የከተማ ግብርናን በሁሉም ክፍለ ከተሞች በማስፋፋትና የምርት አቅርቦትን በማሳደግ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስና የገበያ መረጋጋትን ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። 

‎‎እስካሁን በተከናወኑ ተግባራትም በአቅርቦት ረገድ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን አስታውቀዋል።

‎‎ይህ ውጤት ሊገኝ የቻለው በሁሉም አካላት የተቀናጀ ርብርብ መሆኑን የጠቆሙት ምክትል ከንቲባው፤ በቀጣይም ዘርፉን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በትጋት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል። 


 

‎ጠንክሮ በመስራት ከራስ ፍጆታ ባለፈ ለማህበረሰቡ የሚሆን ምርት ማምረት እንደሚቻል ጠቅሰው የከተማ አስተዳደሩ ለዘርፉ መጠናከርና ለተሳታፊዎች ማበረታቻ የሚሆኑ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

‎‎የዛሬው የድጋፉ ተጠቃሚዎችም በዘርፉ ጠንክረው በመስራት ከራስ ፍጆታ ባሻገር ማማረት እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤ በበኩላቸው፤  ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች በከተማ ግብርና በቀጥታ ተጠቃሚ መሆናቸውን አመልክተዋል። 


 

‎የከተማ ግብርና መርሃግብር ዜጎችን ከሸማችነት ወደ አምራችነት እንዲሻገሩ በማስቻል ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የሚተርፉ ማድረጉ የዘርፉን ስኬት የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል። 

‎መርሐ ግብሩ በከተማ ደረጃ የግብርና ስራ መስራትና ውጤታማ መሆን እንደሚቻል በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን ተናግረዋል።

‎የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ምስክር ነጋሽ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በክፍለ ከተማው ነዋሪዎችን በከተማ ግብርና ተጠቃሚ የሚያደርጉ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።


 

‎የድጋፉ ተጠቃሚዎች በበኩላቸው፤ የተደረገላቸውን ድጋፍ በአግባቡ በመጠቀም ከራሳቸው ፍጆታ አልፈው ምርታቸውን ለሌሎች ተደራሽ ለማድረግ በትጋት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም