ቀጥታ፡

በዝምባብዌ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የተመራ  ልዑክ የተለያዩ ተቋማትን ጎበኘ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦በዝምባብዌ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሉክ ማላባ የተመራ የሀገሪቷ ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎብኝቷል።

የተቀናጀ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የዜጎች ተጠቃሚነት ማጎልበቻ ሆነዋል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

በዚህም በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ  ኢንስቲትዩት እና በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የስራ ሀላፊዎች ለጎብኚዎቹ ገለጻና ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል።


 

የዝምባብዌ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሉክ ማላባ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በሕግ ዘርፍ ውስጥ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በጉብኝታቸው ወቅት ገልጸዋል።

አገራቸው የፍትሕ ሥርዓቱን ውጤታማነትና ቅልጥፍና ለማሳደግ ቴክኖሎጂን ለመጠቀም ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

ቴክኖሎጂን መጠቀም የፍርድ ቤቶችን የአሠራር ቅልጥፍና ከማሳደጉም በላይ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እንደሚረዳ ጠቁመዋል።

በዚህ ረገድ፣ ጉብኝቱ የልዑካን ቡድኑ ከኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ሂደትና ተሞክሮ እንዲማሩ ትልቅ ዕድል እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።


 

በተጨማሪም የዝምባብዌ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።


 

ስምምነቱን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ቴዎድሮስ ምህረት እና የዝምባብዌ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሉክ ማላባ ተፈራርመውታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም