ቀጥታ፡

በዞኑ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው

መቱ ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦በኢሉአባቦር ዞን የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ተግባራት ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ እየተከናወኑ መሆኑን በብልጽግና ፓርቲ የዞኑ ሴቶች ክንፍ ገለጸ።

በግብርናው ዘርፍ የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ

በብልጽግና ፓርቲ የኢሉአባቦር ዞን ሴቶች ክንፍ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፓርቲውን ማኒፌስቶ እና የመወዳደሪያ ምልክት ለሴት አባላትና ደጋፊዎች ይፋ አድርጓል። 

በብልጽግና ፓርቲ የዞኑ ሴቶች ክንፍ ኃላፊ ወይዘሮ አለምነሽ ቡላ እንደገለጹት፤ ፓርቲው የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሻግሩ ተግባራትን በልዩ ትኩረት እያከናወነ ይገኛል።


 

በዞኑ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ ጥረት ተደርጓል ብለዋል።

የሀገር ዕድገትና ተጠቃሚነት ያለ ሴቶች ንቁ ተሳትፎ ሙሉ ሊሆን እንደማይችል የገለጹት ኃላፊዋ፤ በቀጣይም ፓርቲው የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማሳደግ አበክሮ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የቢሎ ኖጳ ወረዳ ሴቶች ክንፍ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ሎሚ ሐቢብ በበኩላቸው፤ በወረዳው የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን አውስተዋል። 


 

በቀጣይም እነዚህን ስኬቶች በማጠናከር፣ ሴቶች ለራሳቸውና ለሀገራቸው ዕድገት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ በትጋት እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል ወይዘሮ ገበያነሽ ገዛኸኝ እና ወይዘሮ ደራርቱ ሞሲሳ፤ በአሁኑ ወቅት ሴቶች በፖለቲካ አመራርነትና በውሳኔ ሰጪነት ያላቸው ተሳትፎ የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰዋል። 


 

ይህንኑ ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግና የሴቶችን ድምፅ ለማጎልበት በጠቅላላ ምርጫው የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም አክለዋል።

የምርጫ ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆንም የምርጫ ሥነ-ምግባርን ባከበረ መልኩ የመምረጥና የመመረጥ መብታቸውን በመጠቀም ለሀገር ግንባታ የበኩላቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም