ቀጥታ፡

ለሀገር ሰላምና እድገት ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችለንን ካርድ ወስደናል

ደብረ ብርሃን፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ተጠቅመን ለሀገር ሰላምና እድገት ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችለንን ካርድ ወስደናል ሲሉ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

ምርጫ ህዝብ የስልጣን ባለቤት መሆኑ በተግባር የሚረጋገጥበት ነው

በመጪው ግንቦት ወር ለሚካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል ።

ይህንኑ ተከትሎ ኢዜአ በደብረ ብርሀን ከተማ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገር ሰላምና እድገት ይበጃል ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ የሚያስችላቸውን ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ ፍርዴ ወርቄ  ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ስርአት መገለጫ መሆኑን ተናግረዋል።


 

በዚህም በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ለሀገር ሰላምና እድገት ይበጃል ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

በደብረ ብርሃን ምርጫ ክልል 02 ምርጫ ጣቢያ “ሀ"-1 ለመራጭነት ተመዝግበው ካርድ መውሰዳቸውን ገልጸዋል።

በምርጫ የሚመሰረት መንግስት ሰላምና ልማትን ያረጋግጣል ብዬ ስለማምን በዘንድሮው ምርጫ ለመሳተፍ ተመዝግቤ ካርድ ወስጃለሁ ያሉት ደግሞ ሌላው የ70 ዓመት ዕድሜ ያላቸው አቶ ጌታቸው በቀለ ናቸው።

ምዝገባው በዲጂታል ጭምር ታግዞ መካሄዱ ሂደቱን እንዳቀለለው ጠቁመው የወሰዱትን ካርድ ተጠቅመው በምርጫው ቀን ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።


 

ለሀገር ልማትና ሰላም ግንባታ ይበጃል ያልኩትን የፖለቲካ ፓርቲ ለይቼ ለመምረጥ የሚያስችለኝን የመራጭነት ካርድ በመውሰዴ ተደስቻለሁ ያሉት ደግሞ ወይዘሮ አዲስ መላኩ ናቸው።

ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በአካባቢያቸው የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማበርከት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም