ለሀገርና ህዝብ ይጠቅማል የምንለውን ፓርቲ መምረጥ የሚያስችለንን የምርጫ ካርድ እየወሰድን ነው - ነዋሪዎች - ኢዜአ አማርኛ
ለሀገርና ህዝብ ይጠቅማል የምንለውን ፓርቲ መምረጥ የሚያስችለንን የምርጫ ካርድ እየወሰድን ነው - ነዋሪዎች
ሰመራ፤ የካቲት 28/2018(ኢዜአ)፦ ለሀገርና ህዝብ ይጠቅማል የምንለውን ፓርቲ መምረጥ የሚያስችለንን የምርጫ ካርድ እየወሰድን ነው ሲሉ በሠመራ ሎጊያ የምርጫ ካርድ የወሰዱ ነዋሪዎች ተናገሩ።
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች መራጮች የምርጫ ካርድ መውሰድ ጀምረዋል
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከዛሬ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በየምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ መካሄድ ጀምሯል።
በዚሁ መርሃ ግብር መሰረትም የኢዜአ ሪፖርተር በሠመራ ሎጊያ የምርጫ ጣቢያዎች በመዘዋወር የምርጫ ካርድ ሲወስዱ ያገኛቸውን ነዋሪዎች አነጋግሯል።
አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎችም ለሀገርና ህዝብ ይጠቅማል የምንለውን ፓርቲ መምረጥ የሚያስችለንን የምርጫ ካርድ እየወሰድን እንገኛለን ብለዋል።
በምርጫው ሂደት ዴሞክራሲያዊ መብትን መጠቀም የሚቻለው የምርጫ ካርድ ሲወሰድ መሆኑን አንስተው ለዚህም ጊዜ ሳናባክን በመጀመሪያው እለት ወስደናል ነው ያሉት።
በምርጫ ጣቢያዎቹ ካነጋገርናቸው የሠመራ ከተማ ነዋሪዎች መካከል አፍክኤ ዓሊ፣ መሐመድ ያዬ እና ወጣት ሃቢብ መሐመድ፤ ሀገርን ሊያስተዳድርና ህዝብን ሊጠቅም ይችላል የምንለውን ፓርቲ መምረጥ የሚያስችለንን ካርድ ወስደናል በዚህም ተደስተናል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የአፋር ክልል ምርጫ ቦርድ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት የዱብቲ ምርጫ ክልል ኀላፊ ኢብራሂም አብደላ፤ በምርጫ ክልሉ 124 ምርጫ ጣቢያዎች ዝግጁ ሆነው ማስተናገድ ጀምረዋል ብለዋል።
በምርጫ ጣቢያዎቹ በድምሩ 496 የምርጫ አስፈፃሚዎች መራጮችን ከዛሬ ጀምሮ ለማስተናገድ በተሟላ ዝግጁነት ላይ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።