ብልጽግና ፓርቲ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ በሀገር ጉዳይ አካታችና አሳታፊ ስርዓት ዘርግቷል - ኢዜአ አማርኛ
ብልጽግና ፓርቲ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ በሀገር ጉዳይ አካታችና አሳታፊ ስርዓት ዘርግቷል
ሀዋሳ፤ የካቲት 28/2018(ኢዜአ)፦ ብልጽግና ፓርቲ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ በሀገሩ ጉዳይ አካታችና ሁሉንም አሳታፊ ያደረገ ስርዓት መዘርጋቱን የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ጥራቱ በየነ ገለጹ።
ኢትዮጵያን የሚገነባት እና የሚያጸናት የተደመረ ፍላጎትና ሀሳብ ነው - አቶ መለሰ ዓለሙ
ብልፅግና ፓርቲ የማኒፌስቶና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መድረክ በሀዋሳ ከተማ አካሂዷል።
በመድረኩ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ጥራቱ በየነ፤ ብልጽግና ፓርቲ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ በሀገር ጉዳይ አካታችና ሁሉንም አሳታፊ ያደረገ ስርዓት መዘርጋቱን አንስተዋል።
የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት የተፎካካሪ ፓርቲዎች አመራሮች ጭምር በሀገር ጉዳይ ላይ ቀጥታ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ስለመሆናቸው ገልጸዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት አምስት ዓመታት በሁሉም ዘርፎች እመርታዊ ለውጥና ማንሰራራት የታየባቸው የልማት ስራዎችን ማከናወኑንም ጠቅሰዋል።
ፓርቲው ባለፉት አምስት ዓመታት በሁሉም መስኮች የህዝብን ተጠቃሚነት እውን ማድረግ የቻሉ የልማት ስኬቶችን ማስመዝገቡንም ተናግረዋል።
በስንዴ ልማትና ምርታማነት ከራስ አልፎ ለውጭ ገበያ ማቅረብ የተቻለበትን እመርታዊ ለውጥና ማንሰራራት በምሳሌነት አንስተው በሌሎች የግብርና ልማት ስራዎችም የላቀ ስኬት ማምጣት ተችሏል ብለዋል።
ብልጽግና የዲፕሎማሲ፣ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና የምጣኔ ሃብት ስብራቶችን ከመጠገን ባለፈ በኢትዮጵያ ዋልታ ረገጥ እሳቤዎችን በማርገብ ገዥና አሰባሳቢ ትርክት መገንባት ያስቻሉ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል ሲሉ አስረድተዋል።
ፓርቲው በቀጣይ ለላቀ ስኬትና የህዝብ ተጠቃሚነት የሚሰራ መሆኑን አቶ ጥራቱ ገልጸዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የሀዋሳ ከተማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ማራዶና ዘለቀ፤ ብልጽግና በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለህዝቡ የገባውን ቃል መተግበሩን አስታውሰው በቀጣይም ለላቀ ስኬት መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
በለውጡ ዓመታት በተለይም በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ዲጂታላይዜሽን፣ ቱሪዝምና ሌሎችም መስኮች የሚያኮሩ ተግባራት ማከናወኑን ጠቅሰው በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል መሆኑን አንስተው ብልጽግናን መምረጥ የሀገር እድገትንና ስኬትን ማስቀጠል ይሆናል ብለዋል።
በመድረኩ የሀዋሳ ከተማ ማዕከልና የክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎቸ ተገኝተዋል፡፡