ቀጥታ፡

ለመራጭነት የሚያበቃንን ካርድ በመውሰድ ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለመጠቀም ተዘጋጅተናል -የጂንካ ከተማ ነዋሪዎች

ጂንካ፤ የካቲት 28/2018 (ኢዜአ)፦ ለመራጭነት የሚያበቃቸውን የምርጫ ካርድ በመውሰድ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን የጂንካ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር በሚረዱ ፅንሰ ሀሳቦች ላይ ማተኮር ይጠበቅባቸዋል - ምሁራን

አስተያየታቸውን የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች፤ የመራጭነት ካርድ በመውሰድ የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል። 


 

ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ ቦጋለ ታደሰ ቀድመው የምርጫ ካርድ በመውስድ በምርጫው ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

በምርጫ ሂደት የእያንዳንዱ ዜጋ ድምፅ ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም ሰው በምርጫው ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለበትም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሌላው የከተማዋ ነዋሪ አቶ ሰመረ በላይ በበኩላቸው፤ ጠቅላላ ምርጫው ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።


 

በምርጫው ''ይበጀኛል፣ ይወክለኛል፣ ይመራኛል'' የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ የመራጭነት ካርድ ለመውሰድ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

ሴቶች በምርጫው ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በማበረታታት ላይ እንደሚገኙ የተናገሩት ደግሞ ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ፤ ሴቶች በምርጫው እንዲሳተፉ ግንዛቤ የማስጨበጥና የማስተባበር ሥራ እየሠሩ መሆኑን ገልጸዋል። 


 

እሳቸውም ድምፅ ለመስጠት የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ ለመውሰድ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።


 

ወጣት ጌታያውቃል ያለው በበኩሉ ወጣቶች በሀገራቸው ጉዳይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው ጠቅሶ እሱም የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ሚናውን ከመወጣት ባለፈ የመራጭነት ካርድ ለመውሰድ መዘጋጀቱን አስረድቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም