ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ልደታ ክፍለ ከተማ እና ቦሌ ክፍለ ከተማ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 27/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ልደታ ክፍለ ከተማ እና ቦሌ ክፍለ ከተማ ሁለት አቻ ተለያይተዋል። 

በኤፍኤ ካፕ ሊቨርፑል ከዎልቭስ ጋር ይጫወታል

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሰብለወንጌል ወዳጆ እና ይታገሱ ተገኝወርቅ ለልደታ ክፍለ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ቃልኪዳን ሸዋነህ እና ዳሳሽ ሰውአገኝ የቦሌ ክፍለ ከተማን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። 

የልደታ ክፍለ ከተማዋ ሜሮን አበበ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች። 

ውጤቱን ተከትሎ ልደታ ክፍለ ከተማ በ15 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል። ቦሌ ክፍለ ከተማ በ30 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም