ቀጥታ፡

በኤፍኤ ካፕ ሊቨርፑል ከዎልቭስ ጋር ይጫወታል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 27 /2018(ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ አምስተኛ ዙር መርሐ-ግብር ዛሬ ይጀመራል።

በሞልኒው ስታዲየም ዎልቭስ ከሊቨርፑል ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። 

ዎልቭስ በአራተኛው ዙር ግሪምስቢ ታውንን፣ ሊቨርፑል ብራይተንን አሸንፈዋል።

ክለቦቹ በኤፍኤ ካፕ ሲገናኙ የዛሬው ለስድስተኛ ጊዜ ነው።

ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው አምስት ጨዋታዎች ዎልቭስ ሶስት ጊዜ ሲያሸንፍ ሊቨርፑል አንድ ጊዜ ድል ቀንቶታል። በቀሪ አንድ ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል።


 

እ.አ.አ 2023 በውድድሩ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ በተገናኙበት ጨዋታ ሊቨርፑል በድምር ውጤት በማሸነፍ ወደ አራተኛው ዙር ማለፉ የሚታወስ ነው።

ዎልቭስ ኤፍኤ ካፕን አራተኛ ጊዜ፣ ሊቨርፑል ስምንት ጊዜ ዋንጫውን አንስተዋል።

ባለሜዳው ዎልቭስ ለመጨረሻ ጊዜ ውድድሩን ያሸነፈው እ.አ.አ በ1960 ነው። 

ሊቨርፑል የመጨረሻውን ዋንጫ ያነሳው እ.አ.አ በ2022 መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

ሁለቱ ቡድኖች በሳምንቱ አጋማሽ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሳምንት ባደረጉት ጨዋታ ዎልቭስ በሜዳው 2 ለ 1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

በቀናት ልዩነት በኤፍኤ ካፑ ይገናኛሉ።

የ32 ዓመቱ ፋራይ ሃላም ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።

የኤፍኤ ካፕ የአምስተኛ ዙር መርሐ ግብር እስከ የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

ጨዋታውን የሚያሸንፉ ክለቦች ወደ ሩብ ፍጻሜ ያልፋሉ።

ኤፍኤ ካፕ 155 ዓመታትን ያስቆጠረ አንጋፋ የክለቦች ውድድር ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም