ቀጥታ፡

የሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ይጫወታል 

አዲስ አበባ፤ የካቲት 27/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል።

ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ።

በኤፍኤ ካፕ ሊቨርፑል ከዎልቭስ ጋር ይጫወታል

ድሬዳዋ ከተማ በሊጉ ካደረጋቸው 16 ጨዋታዎች መካከል ስድስቱን ሲያሸንፍ ዘጠኝ ጊዜ ተሸንፏል። አንድ ጊዜ ደግሞ ነጥብ ተጋርቷል። 15 ግቦችን በ16ቱ ጨዋታዎች ላይ ሲያስቆጥር 24 ግቦችን አስተናግዷል። 

ቡድኑ በ19 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።

ተጋጣሚው ኢትዮ ኤሌክትሪክ  በሊጉ ባከናወናቸው 16 ጨዋታዎች 14ቱን አሸንፏል። አንድ  ጊዜ ሲሸነፍ በተመሳሳይ አንድ ጊዜ አቻ ወጥቷል። 36  ግቦችን በጨዋታዎቹ ላይ ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ሰባት ጎሎች ተቆጥረውበታል። 

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ43 ነጥብ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። 

ሁለቱም ቡድኖች ተከታታይ ድላቸውን ለማስመዝገብ ይጫወታሉ። ኢትዮ ኤሌክትሪክ ካሸነፈ የሊጉን መሪነት ያጠናክራል።

በሌላኛው መርሐ-ግብር ይርጋጨፌ ቡና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። 

አዲስ አዳጊው ይርጋጨፌ ቡና በሊጉ ባከናወናቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች ሁለቱን ሲያሸንፍ ዘጠኝ ጊዜ ተሸንፏል። በቀሪ አምስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል። በጨዋታዎቹ ላይ 7 ግቦችን ሲያስቆጥር 22 ጎሎች ተቆጥረውበታል። 

ይርጋጨፌ ቡና በ11 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።

ተጋጣሚው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሊጉ ባደረጋቸው 16 ጨዋታዎች በ13ቱ አሸንፎ በአንዱ ተሸንፎ ሁለት ጊዜ አቻ ወጥቷል። ቡድኑ 42 ግቦችን ሲያስቆጥር አምስት ጎሎች አስተናግዷል። 

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ41 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። 

ልደታ ክፍለ ከተማ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ልደታ ክፍለ ከተማ በ14 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል። ቦሌ ክፍለ ከተማ በ29 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ለይ ተቀምጧል። 

ሁለቱም ቡድኖች በድል ጉዟቸው ለመቀጠል የሚያደርጉት ጨዋታ ተመጣጣኝ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት እስከ የካቲት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል። 

የኢትዮ ኤሌክትሪኳ ዳግማዊት ሰለሞን በ18 ግቦች የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እየመራች ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ ረድኤት አስረሳኸኝ በ12 ግቦች ቀጣዩን ደረጃ ይዛለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም