በስፔን ጥሎ ማለፍ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ሪያል ሶሲዬዳድ ከአትሌቲኮ ቢልባኦ የመልስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ - ኢዜአ አማርኛ
በስፔን ጥሎ ማለፍ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ሪያል ሶሲዬዳድ ከአትሌቲኮ ቢልባኦ የመልስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2018 (ኢዜአ)፦ ሪያል ሶሲዬዳድ ከአትሌቲኮ ቢልባኦ በስፔን ጥሎ ማለፍ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታቸውን ዛሬ ያከናውናሉ።
በፕሪሚየር ሊጉ አርሰናል ከብራይተን ማንችስተር ሲቲ ከኖቲንግሃም ፎረስት የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ
ጨዋታው ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በአኖኤታ ስታዲየም ይካሄዳል።
ሁለቱ ቡድኖች የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ በቤናት ቱሪንቴስ ግብ ሪያል ሶሲዬዳድ 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
ሪያል ሶሲዬዳድ ከሜዳው ውጪ ባስመዘገበው ድል በአንጻራዊነት ለፍጻሜ የማለፍ እድል በእጁ ይዟል።
የባስኩ ክለብ ሪያል ሶሲዬዳድ ሁለት ጊዜ የስፔን ጥሎ ማለፍ ዋንጫን አንስቷል። ለመጨረሻ ጊዜ ውድድሩን ያሸነፈው እ.አ.አ በ2019/20 የውድድር ዓመት ነው።
ሌላኛው የባስክ ክለብ አትሌቲኮ ቢልባኦ 24 ጊዜ የስፔን ጥሎ ማለፍ ዋንጫን በማሸነፍ ከባርሴሎና በመቀጠል ስኬታማው ክለብ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።
ቢልባኦ ለመጨረሻ ጊዜ ውድድሩን ያሸነፈው እ.አ.አ በ2023/24 የውድድር ዓመት ነበር።
በደርሶ መልስ የሚያሸንፈው ቡድን በፍጻሜው ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ይገናኛል።
በሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ መርሐ-ግብር አትሌቲኮ ማድሪድ ባርሴሎናን በድምር ውጤት 4 ለ 3 በማሸነፍ ለፍጻሜ አልፏል።