ቀጥታ፡

በፕሪሚየር ሊጉ አርሰናል ከብራይተን ማንችስተር ሲቲ ከኖቲንግሃም ፎረስት የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ 

አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2018 (ኢዜአ)፦‎ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ አምስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ብራይተን ከአርሰናል በአሜክስ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ብራይተን በ37 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል። አርሰናል በ64 ነጥብ የሊጉ አናት ላይ ተቀምጧል።

ጨዋታው ብራይተን ሶስተኛ ተከታታይ የሊግ ድሉን ለማስመዝገብ የሚያደርገው ነው።

ተጋጣሚው አርሰናል ካሸነፈ የሊጉን መሪነት የሚያጠናክርበት ወሳኝ ሶስት ነጥብ ያገኛል።

የ40 ዓመቱ ክሪስ ካቫናግ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል። 


 

በሌላኛው መርሐ-ግብር ማንችስተር ሲቲ ኖቲንግሃም ፎረስትን ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ላይ በኢትሃድ ስታዲየም ያስተናግዳል።

አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ማንችስተር ሲቲ በ59 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

ኖቲንግሃም ፎረስት በ27 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዟል። 

ማንችስተር ሲቲ ማሸነፍ በዋንጫ ፉክክሩ ላይ እንዲቀጥል ያደርገዋል።

ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች ያላሸነፈው ኖቲንግሃም ፎረስት ማሸነፍ ላለመውረድ በሚያደርገው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ ያስገኝለታል።

የ40 ዓመቱ ዳረን ኢንግላንድ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።


 

ምሽት 5 ሰዓት ከ15 ላይ ኒውካስትል ዩናይትድ ከማንችስተር ዩናይትድ ይጫወታል።

ኒውካስትል ዩናይትድ በ36 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ማንችስተር ዩናይትድ በ51 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

ኒውካስትል ከሁለት ተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል።

በማይክል ካሪክ ስር ድንቅ ግስጋሴ እያደረገ የሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድ በመልካም ጉዞው ለመቀጠል እና የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ፉክክሩን ለማጠናከር ሶስት ነጥብ ማግኘት ወሳኝ ነው።


 

በቪላ ፓርክ ስታዲየም አስቶንቪላ ከቼልሲ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ላይ ይጫወታሉ።

አስቶንቪላ በ51 ነጥብ አራተኛ፣ ቼልሲ በ45 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ የሚፎካካሩት ሁለቱ ቡድኖች ጠንካራ ፍልሚያ ያደጋሉ።

ፉልሃም ከዌስትሃም ዩናይትድ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ላይ በክራቨን ኮቴጅ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም