መቻል ወደ አሸናፊነት መንገድ ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
መቻል ወደ አሸናፊነት መንገድ ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 24/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 22ኛ ሳምንት ዛሬ ተጀምሯል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መቻል ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ዩጋንዳዊው ቻርልስ ሙሲጌ እና ዓለምብርሃን ይግዛው ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ከአራት የሊግ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው መቻል በ34 ነጥብ ደረጃውን ከስድስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉ ዘጠነኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በውድድር ዓመቱ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ24 ነጥብ ከነበረበት 13ኛ ደረጃ ወደ 12ኛ ዝቅ ብሏል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ-ግብር ቅዲስ ጊዮርጊስ እና ነገሌ አርሲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ በ25 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሰባት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።
ነገሌ አርሲ በ37 ነጥብ ደረጃውን ከሶስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል። አዲስ አዳጊው ቡድን ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።
ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሸገር ከተማ ከኢትዮጵያ መድን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከምድረ ገነት ሽሬ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።