በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 24/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ እና መቻል ነጥብ ተጋሩ
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቢታንያ አስተረፍ እና ምትኬ ብርሃኑ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
የሲዳማ ቡናዋ ምትኬ ብርሃኑ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
በሊጉ ስድስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሲዳማ ቡና በ21 ነጥብ ደረጃውን ከስምንተኛ ወደ ሰባተኛ ከፍ አድርጓል።
በውድድር ዓመቱ ስምንተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዳማ ከተማ በ16 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።