በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ እና መቻል ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ እና መቻል ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 24/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ16ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሸገር ከተማ እና መቻል ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዓይናለም አለማየሁ እና ቤተልሄም ታምሩ ለሸገር ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ሴናፍ ዋቁማ እና ቤዛዊት ንጉሴ ለመቻል ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
የሸገር ከተማዋ ቤተልሄም ታምሩ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
ውጤቱን ተከትሎ ሸገር ከተማ በ31 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። መቻል በ32 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።