ቀጥታ፡

የዓድዋ ድል ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የብርታት እና የሞራል ምንጭ  ነው - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ 

አዲስ አበባ፤ የካቲት 23/2018(ኢዜአ)፦ የዓድዋ ድል ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የብርታት እና የሞራል ምንጭ  ነው ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።     

130ኛው የዓድዋ ድል በዓል በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተከብሯል።

የዓድዋ ድል ለሠራዊታችን የሁልጊዜም የድል ስንቅ ነው

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዓሉን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የዓድዋ ድል ኢትዮጵያዊያን አንድ ሲሆኑ፤ ምን ያህል ውጤት እንደሚያመጡ ያመላከተ ነው ብለዋል።    


 

ዓድዋ የቅኝ ግዛት ቀንበር የተሰባበረበት፤ "ጥቁሮች አይችሉም" የሚለውን አስተሳሰብ የሰበረ ታሪካዊ ድል መሆኑንም አንስተዋል።   

አባቶች ያስረከቡንን አገር ለቀጣዩ ትውልድ ለማሻገር የመከላከያ ሰራዊት ከአርበኞች በወረሰው የጀግንነት ወኔ አገርን እየጠበቀ መሆኑን አብራርተዋል።  


 

የዓድዋ ድል ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም መከበር ዘብ ሆኖ በጀግንነት እየተዋደቀ ላለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የብርታትና የሞራል ምንጭ መሆኑንም ነው የገለጹት።  

ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብን ገንብታ እውን ማድረጓን ያስታወሱት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፤ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር ላቀረበችው የባህር በር ጥያቄ መሳካት ህብረትና አንድነት ወሳኝ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም