130ኛው የዓድዋ ድል በዓል "ከአኩሪ ታሪክ፣ ወደ ብሩህ አድማስ" በሚል መሪ ሀሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
130ኛው የዓድዋ ድል በዓል "ከአኩሪ ታሪክ፣ ወደ ብሩህ አድማስ" በሚል መሪ ሀሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 23/2018 (ኢዜአ)፦130ኛው የዓድዋ ድል በዓል "ከአኩሪ ታሪክ፣ ወደ ብሩህ አድማስ" በሚል መሪ ሀሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
የዐድዋ ድል የአንድነት ማሳያ ታሪካዊ ምልክት ነው - የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን
በክብረ በዓሉ ላይ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት ተገኝተዋል።
እንዲሁም የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ምክትል ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አምባሳደር ሳልማ ማሊካ ሃዳዲ፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ተገኝተዋል።
በተጨማሪም የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች፣ የሠራዊት አባላት፣ የሀገራት አምባሳደሮች፣ ወታደራዊ አታሼዎችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል።