ቀጥታ፡

ኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የተያዘው ግብ እውን እንዲሆን ወጣቱ በአርበኝነት ስሜት ሊተጋ ይገባል

ሆሳዕና ፤ የካቲት 22/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የተያዘው ግብ እውን እንዲሆን ወጣቱ በአርበኝነት ስሜት ሊተጋ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ብልፅግና ፓርቲ ዋና መገለጫው ለሕዝብ የገባውን ቃል በተግባር በመፈጸም ውጤት ማስመዝገብ ነው

130ኛውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ምክንያት በማድረግ" የዓድዋ አደራ አንድነት፣ ሉዓላዊነትና ማንሰራራት" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ ክልል አቀፍ የወጣቶች መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሄዷል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፣ የዓድዋ ድል የመላው ጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ምልክትና ዓለም አቀፋዊ እውቅና ያለው የታሪክ አሻራ መሆኑን ገልጸዋል።


 

የአሁኑ ዘመን የአርበኝነት ትግል ከድህነት ጋር መሆኑን ጠቅሰው፣ ወጣቱ ይህንን ለማሸነፍ በቁርጠኝነት ሊነሳ ይገባል ብለዋል።

ኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የተያዘው ግብ እውን ሊሆን የሚችለው ወጣቱ በታታሪነትና በአርበኝነት ስሜት ሲሰራ መሆኑንም አመልክተዋል።

የክልሉ የወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ ጌታቸው ሌሊሾ በበኩላቸው፣ የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያንን በአንድነት ጥላ ስር በማሰባሰብ የተገኘ አኩሪ ገድል ነው ብለዋል።

የምክክር መድረኩ ዋና ዓላማ የዓድዋን ስኬት በወጣቱ ውስጥ ማስረጽና ወጣቱን የታሪክ ባለቤትና የልማት ኃይል ማድረግ ነው ብለዋል።


 

ወጣቶች ቀደምት አባቶች በዓድዋ የከፈሉትን መስዋዕትነትንና የተገኘውን ድል በክልሉ ፈጣንና ሁለንተናዊ ዕድገት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የራሳቸውን አሻራ በማኖር ሊደግሙ ይገባል ብለዋል።፡

በመድረኩ የተሳተፉ ወጣቶች የቀደምት አባቶችን የዓድዋ ድል መስዋዕትነት በልማት ለመድገም ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል።

ወጣት አብዱወሀብ ኑረዲን፤ ከጀግኖች አባቶች የተረከብናትን ሀገር ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ገዢ ትርክትን መገንባትና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከር የወቅቱ አርበኝነት ነው ሲል ተናግሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም