ቀጥታ፡

የዓድዋ ድል ለአትሌቶች የአሸናፊነትና አይበገሬነት ወኔ መነሻ ሆኗል

ደብረ ብርሃን ፤ የካቲት 22/2018 (ኢዜአ)፦  የዓድዋ ድል ለአትሌቶች የአሸናፊነትና አይበገሬነት ወኔ መነሻ መሆኑ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የቀጣይ ስምንት ወራት ዐበይት የትኩረት ጉዳዮች

130ኛ ዓመት የዓድዋ ድል በዓልን አስመልክቶ በደብረ ብርሃን ከተማ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ተካሂዷል።

የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ወርቃለማሁ ኮስትሬ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፣ የዓድዋ ድል ሀገር በትውልዶች ቅብብሎሽ የምትገነባ መሆኗን በተግባር ያስተማረ ነው።


 

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም አደባባይ በሚያደርጓቸው ውድድሮች ለማሸነፍ የሚያሳዩት የአልበገር ባይነት ወኔ መነሻ የዓድዋ ድል መሆኑን አንስተዋል።

ወጣቶች ከዓድዋ ታሪካዊ ድል በመማር የአካባቢያቸውን ሰላም እንዲጠብቁና  በልማት ሥራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ ድህነትን ለማሸነፍ በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

የሸዋ አትሌቶች ማሕበር ሊቀመንበር እንዳለ ታደሰ፣ አትሌቶች በዓለም አቀፍ ውድድሮች የሚያሳዩት አይበገሬነትና የአሸናፊነት ወኔ ምንጩ የዓድዋ ድል መሆኑን አመልክተዋል።


 

በዓሉን የሚዘክረው የጎዳና ላይ ሩጫ የድሉን መልካም እሴት ለወጣቱ በማስገንዘብ ሁሉም በተሰማራበት ሙያ ለአሸናፊነት እንዲዘጋጅ የሚያነሳሳ ነው ብለዋል።

በዕለቱ በወንድና በሴት አትሌቶች የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር የተካሄደ ሲሆን የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችም በ3 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫው ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም