ቀጥታ፡

ብሔራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል በሸገር ከተማ በሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የመስክ ምልከታ እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 22/2018 (ኢዜአ)፦ ብሔራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል በሸገር ከተማ በሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የመስክ ምልከታ እያደረገ ነው።

በአዲስ አበባ ለአምራች ኢንዱስትሪ ምርታማነት የተሰጠው ትኩረት አመርቂ ውጤት አስገኝቷል

በመስክ ምልከታው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪና የካውንስሉ ሰብሳቢ አምባሳደር ግርማ ብሩ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍስሐ ይታገሱ (ዶ/ር) እና የካውንስሉ አባል ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።


 

የመስክ ምልከታው የአምራች ኢንዱስትሪዎች ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ መቃኘትና እያጋጠሙ ለሚገኙ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል።

ብሔራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል የዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ፣ የማምረት አቅም ችግሮችና ማነቆዎችን በመለየት መፍትሔ ለመስጠት የተቋቋመ ነው።

ካውንስሉ ከዚህ ቀደም በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን የሥራ እንቅስቃሴ መመልከቱ ይታወሳል።

አምራቾች በፋይናንስ፣ በኃይል አቅርቦት፣ በመሰረተ ልማት፣ በግብዓትና በአሠራር ለሚያጋጥማቸው ችግር ተግባራዊ ምላሽ በመስጠት ለምርትና ምርታማነት ማደግ እየሠራ እንደሚገኝም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም