ማንችስተር ሲቲ ወሳኝ ድል አሳክቷል - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ሲቲ ወሳኝ ድል አሳክቷል
አዲስ አበባ ፤ የካቲት 21/2018 (ኢዜአ)፡- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት ማንችስተር ሲቲ ሊድስ ዩናይትድን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በኢላንድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አንቶዋን ሴሜኒዮ በመጀመሪያው አጋማሽ ማብቂያ የማሸነፊያ ግቧን አስቆጥሯል።
በሊጉ 18ኛ ድሉን ያስመዘገበው ማንችስተር ሲቲ በ59 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ዝቅ አድርጓል።
ይህን ተከትሎም በዋንጫ ፉክክሩ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 11ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሊድስ ዩናይትድ በ31 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የሊጉ መሪ አርሰናል ነገ ከቼልሲ ጋር የሚያደርገው የደርቢ ጨዋታ ይጠበቃል።