ቀጥታ፡

ሊቨርፑል ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል 

አዲስ አበባ ፤ የካቲት 21/2018 (ኢዜአ)፡- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት ማምሻውን ሶስት ጨዋታዎች ተደርገዋል።

ሊቨርፑል ዌስትሃም ዩናይትድን 5 ለ 2 ረቷል።

በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሁጎ ኢኪቲኬ፣ ቨርጂል ቫን ዳይክ፣ አሌክሲስ ማካሊስተር፣ ኮዲ ጋፕኮ እና የዌስትሃሙ አክሴል ዲሳሲ በራሱ ላይ ለቀያዮቹ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል። 

ቶማስ ሶቼክ እና ቫለንቲን ካስቴላኖስ ለዌስትሃም ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

በሊጉ 14ኛ ድሉን ያስመዘገበው ሊቨርፑል በ48 ነጥብ ደረጃውን ከስድስተኛ ወደ አምስተኛ ከፍ አድርጓል። 

የወቅቱ የሊጉ የዋንጫ ባለቤት ሊቨርፑል በሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ በሚያደርገው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 15ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ዌስትሃም ዩናይትድ በ25 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

በሌሎች ጨዋታዎች ብሬንትፎርድ በርንሌይን 4 ለ 3፣ ኤቨርተን ኒውካስትል ዩናይትድን 3 ለ 2 አሸንፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም