ኢትዮጵያ ቡና ደረጃውን ያሻሻለበትን ድል አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ቡና ደረጃውን ያሻሻለበትን ድል አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2018 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ኢትዮጵያ ቡና ነገሌ አርሲን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ራምኬል ጀምስ በ87ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።
በሊጉ ሰባተኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮጵያ ቡና አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ26 ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 9ኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 5ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ነገሌ አርሲ በ36 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ-ግብር መቻል እና መቀሌ 70 እንደርታ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
መቀሌ 70 እንደርታ በ22 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። መቻል በ31 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።
ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ የ21ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ወላይታ ድቻ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 0 ሲረታ አዳማ ከተማ እና ሸገር ከተማ ሶስት አቻ ተለያይተዋል።