ቀጥታ፡

ሴቶች በተለያየ መስክ ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሰመራ፤ የካቲት 19/2018 (ኢዜአ)፡-   የሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ውጤት እያመጡ መሆናቸውን የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ምክር ቤት አባል ወይዘሮ ተስፋነሽ አበራ ተናገሩ።

በዞኑ በጤና ጣቢያዎች ደረጃ መሰጠት የጀመረው በቀዶ ሕክምና የማዋለድ አገልግሎት የእናቶችና ህጻናትን ጤና ለማሻሻል አግዟል

በብልጽግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት "በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሐሳብ የሴቶች ንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ነው።


 

በመድረኩ ላይ የተገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና በብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ምክር ቤት አባል ወይዘሮ ተስፋነሽ አበራ፤ፓርቲው የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያከናወናቸው ተግባራት ስኬታማ ናቸው ብለዋል።


 

ሴቶች እንደ ሀገር በመጣው ለውጥ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀው ፓርቲው ውስብስብ የሆኑ ማነቆዎችን በመሻገር እመርታዊ ድሎችን ማስመዝብ መቻሉንም ተናግረዋል።

በተለይም ዕድሎችን አሟጦ በመጠቀም ሴቶችን በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ በማሳተፍ የሚታዩ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሉንም ነው የጠቀሱት።

በብልፅግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን በበኩላቸው ያለ ሴቶች ተሳትፎ የሚሳካ አንዳችም ተግባር እንደሌለ በማመን የሴቶችን ተሳታፊነት ከመቼውም ጊዜ በላይ ማሳደግ ተችሏል ነው ያሉት።


 

የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሚናቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

በአፋር ክልል የሚገኙ የሴቶች አደረጃጀቶችን በመጠቀም በየደረጃው ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን የተናገሩት ደግሞ በብልፅግና ፓርቲ የአፋር ክልል ሴቶች ክንፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኡርቲያይ ያይሶ ናቸው።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም