አያቶቻችን በጠንካራ አንድነትና መስዋዕትነት ሉዓላዊ ሀገር እንዳስረከቡን ሁሉ ትውልዱም ተባብሮ ሀገሩን ማበልጸግ ይጠበቅበታል - ኢዜአ አማርኛ
አያቶቻችን በጠንካራ አንድነትና መስዋዕትነት ሉዓላዊ ሀገር እንዳስረከቡን ሁሉ ትውልዱም ተባብሮ ሀገሩን ማበልጸግ ይጠበቅበታል
ድሬደዋ፤ የካቲት 19/2018 (ኢዜአ)፡- አያቶቻችን በመስዋዕትነት ሉዓላዊ ሀገርን እንዳስረከቡን ሁሉ ትውልዱም ወደ ብልጽግና የተሻገረች ሀገርን ለቀጣዩ ለማውረስ በቁርጠኝነት መትጋት አለበት ሲሉ የድሬዳዋ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የታሪክ መምህራን ተናገሩ።
የዓድዋ ድልን አስመልክተው የድሬደዋ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የታሪክ መምህራን ሄኖክ ሲማ እና ገብረ መድህን ታደሰ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓድዋ ድል ኢትዮጵያ ለጥቁር ህዝቦች ነፃነት ችቦ የለኮሰችበት ዘመን የማይሽረው ደማቅ ታሪክ ነው።
የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን በጋራ ቆመው የሀገር ክብርና ሉዓላዊነት ያስጠበቁበት የመላ ጥቁር ህዝቦች የአሸናፊነት ምልክት ነው
በአያቶች የተመዘገበውን ደማቅ ታሪክ ትውልዱ የትኛውንም መስዋዕትነት በመክፈል ሊጠብቀው እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የዓድዋን ህያው ታሪክ በአግባቡ እየተማረ የሚገኘው አገር ገንቢውና ተረካቢው ትውልድ በአገር መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ማፅናት እና በጋራ መቆም ያለውን ወሳኝ ሚና በአግባቡ እየተረዳ መሆኑን አንስተዋል።
የአባቶቹን ወኔ በመላበስ በአንድነት ድህነትንና ልመናን ከአገር ለማጥፋት የተጀመረውን ጉዞ በማሳካት የራሱን ተሻጋሪ ታሪክ መፃፍ እንዳለበት ነው ያስገነዘቡት ።