ቀጥታ፡

አትሌቲኮ ማድሪድ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 18/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ አትሌቲኮ ማድሪድ ክለብ ብሩዥን 4 ለ 1 አሸንፏል።

በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አሌክሳንደር ሶርሎዝ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል።

ጆኒ ካርዶሶ ቀሪዋን ጎል ለአትሌቲኮ ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ጆኤል ኦርዶኔዝ ለክለብ ብሩዥ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።



ክለብ ብሩዥ በመጀመሪያው አጋማሽ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ በሁለተኛው አጋማሽ ብልጫ ወስደው ተጫውተዋል።

ጨዋታውን ተከትሎ አትሌቲኮ ማድሪድ በደርሶ መልስ ውጤት 7 ለ 4 በማሸነፍ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም