ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ሀገር ያጸኑ ጀግኖች ምድር ናት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 

አዲስ አበባ፤ የካቲት 14/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ በትውልድ ቅብብሎሽ ሀገር ያጸኑ የበርካታ ጀግኖች ምድር ናት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ተጠናቀቀ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ በትውልድ ቅብብሎሽ ሀገር ያጸኑ የበርካታ ጀግኖች ምድር መሆኗን አስገንዝበዋል።


 

የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች እዝም ባለፉት 65 ዓመታት በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ የማይበገር ጽናት ይዞ ኢትዮጵያን ያኮራ ጀብዱ ፈጽሟል ብለዋል። 

እዙ አሁን ላይ በመከላከያ ሪፎርም ስራዎች አማካኝነት አየር ወለድ፣ ኮማንዶ እና ልዩ የጸረ ሽብር ኃይል መያዙንም አመላክተዋል።

በዚህም መሠረት በአደረጃጀት፣ በሰው ኃይል እና በትጥቅ ዘመኑን በዋጀ መልኩ መዋቀሩን ነው ያስታወቁት።


 

በመሆኑም በየትኛውም ጊዜና በማንኛውም ሁኔታ እዙ ግዳጁን በብቃት ለመፈጸም በአስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል ሲሉ አረጋግጠዋል።

እዙ 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ሲያከብር የገነባውን የዘመነ ወታደራዊ አቅም፣ የሰው ኃይል ዝግጁነት እና የታክቲክ ብቃት ለሕዝብ ይፋ አድርጓል ብለዋል።


 

 በተለይም ዛሬ የቀረበው የተቀናጀ የውሃ ላይ ልምምድ፣ የአየር ወለድና የኮማንዶ አባላት በቅንጅት ያሳዩት ልዩ ልዩ ወታደራዊ ክህሎት የሠራዊቱን ከፍተኛ ብቃት ያረጋገጠ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም