ቀጥታ፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የዕጩዎች የስነ ምግባር ደንብን ፈረሙ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 14/2018 (ኢዜአ)፡- የፖለቲካ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያዘጋጀውን የዕጩዎች የስነ ምግባር ደንብ ፈረሙ።

ምርጫ ቦርድ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመወዳደር የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመወዳደሪያ ምልክት ይፋ አደረገ

የስነ ምግባር ደንቡ ምርጫው ስነ ምግባርን በተላበሰ መልኩ በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የቦርዱ ስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና ተወካዮች እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች ተኝተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በዚሁ ወቅት፥ ቦርዱ ፓርቲዎች ክርክር አድርገው አማራጭ ሃሳባቸውን ለህዝቡ የሚያቀርቡበት መር ሃግብር እየተዘጋጀ ነው ብለዋል።

መራጩ ህዝብ በእውቀት ላይ ተመስርቶ ምርጫ እንዲያደርግ ከፓርቲዎች ብዙ ስራ ይጠበቃል ያሉት ሰብሳቢዋ፥ መገናኛ ብዙኃንም ለተወዳዳሪ ፓርቲዎች እኩል የአየር ሰዓት በመመደብ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አመልክተዋል።

ምርጫ ቦርድም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የኢዜአ የዲጂታል ሚዲያ ገጾች👉 https://linktr.ee/ENADigital

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም