በተጠባቂው ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ ጋር አቻ ተለያየ - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ ጋር አቻ ተለያየ
አዲስ አበባ፤ ጥር 24/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ24ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ-ግብር ቶተንሃም ሆትስፐርስ እና ማንችስተር ሲቲ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ ፉልሃምን በማሸነፍ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
ማምሻውን በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ራያን ቸርኪ በ11ኛው እና አንቶዋን ሴሜንዮ በ44ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ግቦች ማንችስተር ሲቲ 2 ለ 0 መምራት ችሎ ነበር።
ከእረፍት መልስ ዶምኒክ ሶላንኬ በ53ኛው እና በ71ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋቸው ግቦች ቶተንሃምን አቻ አድርጓል።
በመጀመሪያው አጋማሽ ማንችስተር ሲቲ፣ በሁለተኛው አጋማሽ ቶተንሃም ሆትስፐርስ የተሻለ እንቅስቃሴ አድርገዋል።
የ2 ለ 0 መሪነቱን ማስጠበቅ ያልቻለው ማንችስተር ሲቲ በ47 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። በዋንጫ ፉክክሩ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ጥሏል።
ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ከአራት ወደ ስድስት ከፍ ብሏል።
ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ29 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ የዛሬውን ጨምሮ ባለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።
ዛሬ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ማንችስተር ዩናይትድ ፉልሃምን 3 ለ 2 ሲያሸንፍ ብሬንትፎርድ አስቶንቪላን 1 ለ 0 ረቷል።
ኖቲንግሃም ፎረስት እና ክሪስታል ፓላስ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ24ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ነገ ሰንደርላንድ እና በርንሌይ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጠናቀቃል።