ቀጥታ፡

ማንችስተር ዩናይትድ ፉልሃምን በማሸነፍ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ

አዲስ አበባ፤ ጥር 24/2018 (ኢዜአ)፡- በ24ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ዩናይትድ ፉልሃምን 3 ለ 2 በመርታት ደረጃውን ከነበረበት ወደ አራተኛ ከፍ ያደረገ ሲሆን ሶስተኛ ተከታታይ ድሉንም አስመዝግቧል።


 

የማንችስትር ዩናይትድን ግቦች ካስሚሮ በ19ኛው፣ ኩና በ56ኛው እንዲሁም ሴስኮ በ94ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል።

በአንጻሩ ሂምኔዝ በ85ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት እና ኬቪን በ92ኛው ደቂቃ በጨዋታ ለፉልሃም ግቦችን አስቆጥረዋል።


 

ውጤቱን ተከትሎም ማንችስተር ዩናይትድ በ41 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ዳግም የተረከበ ሲሆን፤ ፉልሃም በ34 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።


 

በሌላ የጨዋታ መርሐ-ግብር ብሬንትፎርድ አስቶንቪላን በሜዳው 1 ለ 0 ሲያሸንፍ፤ ኖቲንግሃም ከክሪስታል ፓላስ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም