ቀጥታ፡

የሊጉ መሪ አርሰናል ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ይጫወታል

አዲስ አበባ፤ ጥር 23/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ24ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል።

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ማጣሪያ መርሐ-ግብር ይፋ ሆነ

በዕለቱ አምስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ሊድስ ዩናይትድ የሊጉን መሪ አርሰናል ምሽት 12 ሰዓት ላይ በኢላንድ ሮድ ስታዲየም ያስተናግዳል።

የዮርክሻየሩ ሊድስ ዩናይትድ በ26 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል። የሰሜን ለንደኑ አርሰናል በ50 ነጥብ የሊጉ አናት ላይ ተቀምጧል።

ባለሜዳው ሊድስ በውድድር ዓመቱ 23 ጨዋታዎችን አድርጎ ስድስት ጨዋታዎችን ሲያሸንፍ ዘጠኝ ጊዜ ሽንፈት አስተናግዷል። በቀሪ ስምንት ጨዋታዎች አቻ ወጥቷል።

ተጋጣሚው አርሰናል በሊጉ ካከናወናቸው 23 ጨዋታዎች መካከል በ15ቱ ድል ሲቀናው በሶስቱ ተሸንፏል። በአምስቱ ጨዋታዎች ላይ ነጥብ ተጋርቷል።

ሊድስ ዩናይትድ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ ከወራጅ ቀጠና ክልል በመጠኑም ቢሆን እንዲርቅ ያደርገዋል።

ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻለው አርሰናል ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል።

መድፈኞቹ ካሸነፉ ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሰባት ከፍ ማድረግ ያስችላቸዋል።




በሌሎች መርሐ-ግብሮች ቼልሲ ከዌስትሃም ዩናይትድ ምሽት 2 ሰዓት ከ30፣ ሊቨርፑል ከኒውካስትል ዩናይትድ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።



ብራይተን ከኤቨርተን እና ዎልቭስ ከቦርንማውዝ በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም