ቀጥታ፡

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ማጣሪያ መርሐ-ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፤ ጥር 22/2018 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ማጣሪያ ተጋጣሚዎች ዛሬ በወጣ ድልድል ተለይተዋል።

በዚሁ መሰረት ቤኔፊካ ከሪያል ማድሪድ፣ ሞናኮ ከወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ፒኤስጂ፣ ካራባግ ከኒውካስትል ዩናይትድ፣ ጋላታሳራይ ከጁቬንቱስ፣ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከአትላንታ፣ ክለብ ብሩዥ ከአትሌቲኮ ማድሪድ፣ ቦዶ ግሊምት ከኢንተር ሚላን እና ኦሎምፒያኮስ ከባየር ሌቨርኩሰን ይጫወታሉ።

የጥሎ ማለፍ ማጣሪያዎቹ በየካቲት ወር የሚካሄዱ ሲሆን በደርሶ መልስ ያሸነፉ ክለቦች ጥሎ ማለፉን ይቀላቀላሉ።

በማጣሪያው የሚሳተፉት ክለቦች በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አዲሱ የውድድር ፎርማት ከ9ኛ እስከ 24ኛ ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁ ናቸው።

ከ36 ክለቦች መካከል በስምንት ጨዋታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ስምንት ቡድኖች በቀጥታ ወደ ጥሎ ማለፉ ገብተዋል።

አርሰናል፣ ባየር ሙኒክ፣ ሊቨርፑል፣ ባርሴሎና፣ ማንችስተር ሲቲ፣ ቼልሲ፣ ቶተንሃም ሆትስፐርስ እና ስፖርቲንግ ሊዝበን በቀጥታ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉ ቡድኖች ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም