ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ሸገር ከተማ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ሸገር ከተማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ጥር 13/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ሸገር ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሄኖክ አዱኛ በ22ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ግብ ሸገር ከተማ መሪ ሆኗል።
ሐዋሳ ከተማ ከነገሌ አርሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው
ጋናዊው ኮንኮኒ ሀፊዝ በ33ኛው ለወልዋሎ የአቻነቷን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ቡልቻ ሹራ ከሸገር ከተማ፣ ሰመረ ሀፍታይ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥተዋል።
ሸገር ከተማ በ16 ነጥብ ደረጃውን ከ17ኛ ወደ 16ኛ ከፍ በማድረግ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል።
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ13 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ሁለቱ ቡድኖች በተመሳሳይ ያለፉትን ሰባት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም።