ቀጥታ፡

ሐዋሳ ከተማ ከነገሌ አርሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው

አዲስ አበባ፤ ጥር 13 /2018 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16 ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ምሽት 12 ሠዓት ሐዋሳ ከተማ ከነገሌ አርሲ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ሐዋሳ ከተማ በሊጉ ባደረጋቸው 15 ጨዋታዎች በሰባቱ አሸንፎ በአራቱ ተሸንፎ በአራቱ አቻ ወጥቷል።  15 ጨዋታዎች 16 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ 10 ጎሎች ተቆጥረውበታል። ቡድኑ 25 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።

ተጋጣሚው ነገሌ አርሲ በሊጉ 15 ጨዋታዎች አከናውኖ ሰባት ጊዜ ድል ሲቀናው በሶስቱ ተሸንፏል። አምስት ጊዜ ደግሞ ነጥብ ተጋርቷል። 17 ግቦችን ሲያስቆጥር 10 ጎሎችን አስተናግዷል።

አዲስ አዳጊው ነገሌ አርሲ 26 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

ጨዋታው ሁለቱ ክለቦች 15 ሳምንት የአቻ ውጤታቸው በኋላ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ነው።

በሌላኛው መርሐ-ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዳማ ከተማ ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እስከ አሁን በሊጉ ማሸነፍ የቻለው ጨዋታ ብዛት ሶስት ብቻ ነው። አራት ጊዜ ሲሸነፍ ስምንት ጊዜ አቻ ወጥቷል። 17 ግቦችን ሲያስቆጥር በተመሳሳይ 17 ጎሎችን አስተናግዷል። ቡድኑ 17 ነጥብ 13 ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ተጋጣሚው አዳማ ከተማ በበኩሉ 15 ጨዋታዎችን አድርጎ አምስት ጊዜ ሲያሸንፍ ሁለት ጊዜ ተሸንፏል። በስምንት ጨዋታዎች ነጥብ ጥሏል። 11 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ 9 ጎሎች ተቆጥረውበታል።

አዳማ ከተማ 23 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 15 ሳምንት መርሐ-ግብር በኢትዮ ኤሌክትሪክ 2 1 ሽንፈት አስተናግዷል።

አዳማ ከተማ ባለፉት ሶስት የሊጉ ጨዋታዎች አቻ ወጥቷል። ሁለቱም ቡድኖች ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታሉ።

ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ምድረ ገነት ሽሬ ከአርባ ምንጭ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ምድረ ገነት ሽሬ 17 ነጥብ 14 ደረጃ ላይ ይገኛል። አርባ ምንጭ ከተማ በስምንት ነጥብ የመጨረሻውን 20 ደረጃ ይዟል።

ምድረ ገነት ሽሬ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዷል። አርባ ምንጭ ከተማ በሊጉ ምንም ጨዋታ ያላሸነፈ ብቸኛው ክለብ ነው።

ጨዋታው ምድረ ገነት ሽሬ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ፣ አርባ ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ሶስት ነጥቡን ለማግኘት የሚያደርጉት ነው።

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከሸገር ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።

በደረጃ ሰንጠረዡ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ 12 ነጥብ 19 ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ሸገር ከተማ 15 ነጥብ 17 ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

ሁለቱም ቡድኖች በተመሳሳይ ባለፉት ስድስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም። ሶስት ነጥብ ለሁለቱም ወሳኝ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም