ኢትዮጵያ መድን እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ መድን እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል
ጨዋታው የተካሄደው በአዲስ አበባ ስታዲየም ነው።
ውጤቱን ተከትሎም የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን በ17 ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 11ኛ ከፍ ማድረግ ችሏል።
በ12 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ፤ ባለፉት ስድስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።