ፋሲል ከነማ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናገደ - ኢዜአ አማርኛ
ፋሲል ከነማ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናገደ
አዲስ አበባ፤ ጥር 2 /2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ፋሲል ከነማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዘላለም አባተ በ62ኛው እና አቡበከር አዳሙ በ74ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሀድያ ሆሳዕና ነጥብ ተጋሩ
በሊጉ አምስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ኢትዮጵያ ቡና በ18 ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 11ኛ ከፍ አድርጓል።
በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ በ25 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። የቡድኑ የ13 ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞ ተገቷል።
ፋሲል ከነማ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ የማድረግ እድሉን ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
በአሁኑ ሰዓት ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ መድን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው።