ቀጥታ፡

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ዛሬ ይጀመራል 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 28/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ዛሬ በዌስትሃም ዩናይትድ እና ኖቲንግሃም ፎረስት መካከል ዛሬ ይደረጋል።

ጨዋታው ምሽት አምስት ላይ በለንደን ስታዲየም ይካሄዳል።

ዌስትሃም ዩናይትድ በ14 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ኖቲንግሃም ፎረስት በ17 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዟል።

የወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ኮትዲቯር ከቡርኪናፋሶ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው

ባለሜዳው ዌስትሃም ዩናይትድ ባለፉት ዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም። 


 

ተጋጣሚው ኖቲንግሃም ፎረስት በበኩሉ ባለፉት አራት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዷል። 

ዌስትሃም ዩናይትድ እና ኖቲንግሃም ፎረስት ወሳኝ ሶስት ነጥብ ለማግኘት ይፋለማሉ።

ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር እርስ በእርስ ባደረጉት ጨዋታ ዌስትሃም ዩናይትድ 3 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። 

ቶኒ ሃሪንግተን ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ጨዋታውን ይመሩታል። 

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት መርሃ ግብር እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም