ቀጥታ፡

ማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪምን አሰናበተ 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 27/2018 (ኢዜአ)፦  ማንችስተር ዩናይትድ የ40 ዓመቱን ፖርቹጋላዊ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪምን ከኃላፊነት ማንሳቱን አስታወቀ። 

አሞሪም ከክለቡ የተለያዩት አመራሮች በሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎች ደስተኛ አለመሆናቸውን ትናንት የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ መሆኑን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል። 

አሰልጣኙ ላለፉት 14 ወራት በዩናይትድ ቤት ቆይተዋል። 

በአፍሪካ ዋንጫ ግብጽ ከቤኒን ናይጄሪያ ከሞዛምቢክ ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ ይጫወታሉ

 

በ3-4-3 የጨዋታ ፍልስፍና ወግ አጥባቂነታቸው ትችት ሲያስተናግዱ የቆዩት አሞሪም ቆይታቸው ውጤታማ አልነበረም።

እ.አ.አ 2024 ከፖርቹጋሉ ስፖርቲንግ ሊዝበን የመጡት አሰልጣኙ ትልቁ ውጤታቸው ባለፈው ዓመት ለዩሮፓ ሊግ ፍጻሜ ደርሰው በቶተንሃም ሆትስፐርስ የተሸነፉበት ነው።

ዩናይትድ አሞሪምን ማሰናበቱን ተከትሎ የ10 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር የውል ማፍረሻ ይከፍላል። 

የክለቡ የቀድሞ ተጫዋች ዳረን ፍሌቸር ክለቡን በጊዜያዊነት ይመራል። ፍሌቸር ከ18 ዓመት በታች ቡድኑ አሰልጣኝ ሆኖ እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ማንችስተር ዩናይትድ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ቋሚ አሰልጣኝ እንደማይቀጥር ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም