ቀጥታ፡

ቤኒን በአፍሪካ ዋንጫው የመጀመሪያ ድሏን አስመዘገበች 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 18/2018(ኢዜአ)፦  በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ አራት ጨዋታ ቤኒን ቦትስዋናን 1 ለ 0 አሸንፋለች። 

በፕሪንስ ሙላይ አብደላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዮሃን ሮቼ በ28ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል። 

በጨዋታው ላይ ቤኒን ብልጫ ወስዳ ተጫውታለች። 

ማንችስተር ሲቲ ኖቲንግሃም ፎረስትን በማሸነፍ የሊጉ መሪ ሆነ

በውድድሩ የመጀመሪያ ድሏን ያስመዘገበችው ቤኒን በሶስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች። 

በአንጻሩ ሁለተኛ ሽንፈቷን ያስተናገደችው ቦትስዋና ያለ ምንም ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

በዚሁ ምድብ ሴኔጋል ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በታንጀር ስታዲየም ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም