ቀጥታ፡

ማንችስተር ሲቲ ኖቲንግሃም ፎረስትን በማሸነፍ የሊጉ መሪ ሆነ 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 18/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ማንችስተር ሲቲ ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በሲቲ ግራውንድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቲጃኒ ራይንደርስ እና ራያን ቼርኪ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።


 

ኦማሪ ሁትቺንሰን ለኖቲንግሃም ፎረስት ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።

በሊጉ 13ኛ ድሉን ያስመዘገበው ማንችስተር ሲቲ በ40 ነጥብ የሊጉን መሪነት ከአርሰናል በጊዜያዊነት ተረክቧል።


 

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኖቲንግሃም ፎረስት በ18 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዟል።

አርሰናል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ከብራይተን የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል። መድፈኞቹ ካሸነፉ የሊጉን መሪነት መልሰው ይረከባሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም