አርሶ አደሮች በበጋ መስኖ በኩታ ገጠም ያለሙትን ስንዴ ውጤታማ ለማድረግ የሰብል እንክብካቤ እያደረጉ ነው - ኢዜአ አማርኛ
አርሶ አደሮች በበጋ መስኖ በኩታ ገጠም ያለሙትን ስንዴ ውጤታማ ለማድረግ የሰብል እንክብካቤ እያደረጉ ነው
መቱ ፤ ታኅሳስ 18/2018 (ኢዜአ)፡- በበጋ መስኖ በኩታ ገጠም ያለሙትን ስንዴ ውጤታማ ለማድረግ የሰብል እንክብካቤ አጠናክረው መቀጠላቸውን በኢሉ አባቦራ ዞን የያዮ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ።
የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የግብአትና ምርጥ ዘርን በወቅቱ ለአርሶ አደሩ ከማድረስ ባለፈ የባለሙያ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ገልጿል።
የያዮ ወረዳ አርሶ አደሮች እንዳመለከቱት፤ የበጋ ስንዴን በመስኖ በኩታ ገጠም በማልማት ስብላቸውን በጋራ እየተንከባከቡ ነው።
የበጋ መስኖ ልማት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታችንን እያሳደገ ነው- አርሶ አደሮች
በግብርና ባለሙያዎች ድጋፍና ግብአት በወቅቱ በማግኘታቸው ጥሩ ምርት እንደሚጠብቁ ገልጸዋል።
ቀደም ባሉት ዓመታት የበጋ መስኖ ልማቱን መተግበራቸውም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንዳሳደገላቸው አውስተዋል።
በበጋ መስኖ መሬታቸውን ደጋግመው በማረስና ግብአትን በአግባቡ በመጠቀም ባለሙት ስንዴ ይበልጥ ውጤታማ ለመሆን የሰብል እንክብካቤ ስራውን አጠናክረው መቀጠላቸውን ተናግረዋል።
የኢሉ አባቦራ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አዳሙ ታከለ እንደገለጹት፤ በዘንደሮ የበጋው ወቅት 120 ሺህ ሄክታር መሬት በስንዴ ለማልማት ታቅዶ በዘር የመሸፈን ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በበጋ ስንዴ ልማቱ እየተሳተፉ ያሉት አርሶ አደሮች ቀደም ብለው ዘርተው የበቀለውን የስንዴ ቡቃያ የመንከባከብ ስራ እያከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የግብአትና ምርጥ ዘርን በወቅቱ ለአርሶ አደሩ ከማድረስ ባለፈ የባለሙያ ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።
በዞኑ አርሶ አደሩ ዝናብን ጠብቆ ከማምረት ወጥቶ በበጋ ስንዴ ልማት ላይ በስፋት በመሰማራት ዓመቱን ሙሉ የማልማት ባሕል እያዳበረ መምጣቱን አንስተዋል፡፡