በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲዳማ ቡናን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲዳማ ቡናን በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 18/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲዳማ ቡናን 5 ለ 0 ረትቷል።
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሸገር ከተማን አሸነፈ
በአበበ በቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ንግስት በቀለ ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር እሙሽ ዳንኤል፣ መሳይ ተመስገን እና ረድኤት አስረሳኸኝ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
በሊጉ 10ኛ ድሉን ያስመዘገበው የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ32 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ከሊጉ መሪ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ዝቅ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና በ18 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።
የቡድኖቹ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ በነበረው ተሳትፎ ምክንያት የተራዘመ ነው።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በያዝነው ሳምንት የመጀመሪያ ተስተካካይ ጨዋታውን ከሸገር ከተማ አድርጎ 2 ለ 1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር መርሃ ግብር መጠናቀቁ ይታወቃል።