በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሸገር ከተማን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሸገር ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 14/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የአንደኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሸገር ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ትዕግስት አዳነ እና ንግስት በቀለ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ገነሜ ወርቁ ለሸገር ከተማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
ውጤቱን ተከትሎ የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ29 ነጥብ ደረጀውን ከአምስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።
በሊጉ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሸገር ከተማ በ27 ነጥብ ከነበረበት አራተኛ ደረጃ ወደ አምስተኛ ዝቅ ብሏል።
የቡድኖቹ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ በነበረው ተሳትፎ ምክንያት የተራዘመ ነው።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቀሪ ተስተካካይ መርሃ ግብሩን ታህሳስ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከሲዳማ ቡና ጋር እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ከተስተካካይ መርሃ ግብሮች ውጪ መጠናቀቁ ይታወቃል።