የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ መድን ጋር አቻ ተለያየ - ኢዜአ አማርኛ
የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ መድን ጋር አቻ ተለያየ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 17/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ሲዳማ ቡና እና ኢትዮጵያ መድን ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ረመዳን በ18ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ኢትዮጵያ መድን መሪ ሆኗል።
ብርሃኑ በቀለ በ29ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል ሲዳማ ቡናን አቻ አድርጋለች።
የሲዳማ ቡናው አጥቂ ሀብታሙ ታደሰ ከእረፍት መልስ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
ውጤቱን ተከትሎ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ነጥቡን ወደ 22 ከፍ አድርጓል። ከተከታዩ ፋሲል ከነማ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ለማስፋት ያገኘውን እድል አልተጠቀመም።
የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን በ13 ነጥብ ደረጃውን ከ16ኛ ወደ 13ኛ ከፍ አድርጓል።
ዛሬ በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ መቻል አዳማ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።
መቻል ከስድስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
ጨዋታዎቹን ተከትሎ የ11ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል።
የ12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከታህሳስ 20 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ እንደሚካሄዱ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።