መቻል ከስድስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
መቻል ከስድስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሃ ግብር መቻል አዳማ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መሐመድ አበራ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር በረከት ደስታ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ተቀይሮ የገባው አህመድ ሁሴን ለአዳማ ከተማ ብቸኛውን ግብ አስቆጥሯል።
ከስድስት የሊጉ ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል የተመለሰው መቻል በ18 ነጥብ ደረጃውን ከዘጠነኛ ወደ አምስተኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ ያሸነፋቸውን ጨዋታዎች ብዛትም አራት አድርሷል።
በአንጻሩ በሊጉ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዳማ ከተማ በ17 ነጥብ ከነበረበት አምስተኛ ደረጃ ወደ ሰባተኛ ዝቅ ብሏል።