ቀጥታ፡

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ መድን የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 17/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጠናቀቃል።

ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድን ከሲዳማ ቡና በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ። 

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን በሊጉ እስከ አሁን ባደረጋቸው 10 ጨዋታዎች በሶስቱ ሲያሸንፍ አራት ጊዜ ተሸንፏል። ሶስት ጊዜ አቻ ወጥቷል።  ስምንት ግቦችን ሲያስቆጥር ዘጠኝ ጎሎችን አስተናግዷል።

ኢትዮጵያ መድን በ12 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል።

ተጋጣሚው ሲዳማ ቡና በበኩሉ በውድድር ዓመቱ 10 ጨዋታዎችን አድርጎ ስድስት ጊዜ ሲያሸንፍ ሽንፈት ያስተናገደው በአንድ አጋጣሚ ነው ። በቀሪ ሶስት ጨዋታዊች አቻ ተለያይቷል። በ10ሩ ጨዋታዎች 13 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ አምስት ግቦች ተቆጥረውበታል።

ሲዳማ ቡና በ21 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው። ካሸነፈ መሪነቱን ያጠናክራል። ኢትዮጵያ መድን ካሸነፈ ደረጃውን ያሻሽላል።  

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቻ ተለያዩ

በሌላኛው መርሃ ግብር  አዳማ ከተማ ከመቻል በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

አዳማ ከተማ በሊጉ ባደረጋቸው 10 ጨዋታዎች አራቱን ሲያሸንፍ አንድ ጊዜ ሽንፈት አስተናግዷል። በአምስቱ ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል። ስድስት ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍ ሶስት ጎሎችን አስተናግዷል። 

ቡድኑ በ17 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል። 

ተጋጣሚው መቻል በሊጉ ካከናወናቸው 10 ጨዋታዎች መካከል ሶስት ጨዋታዎችን ሲያሸንፍ አንድ ጊዜ ተሸንፏል። ስድስት ጊዜ አቻ ወጥቷል። 13 ግቦችን በጨዋታዎቹ ላይ ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ዘጠኝ ግቦች ተቆጥረውበታል። 

በሊጉ በርካታ ጨዋታዎች ላይ ነጥብ ላይ የጣለው  መቻል በተመሳሳይ 15 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም