ቀጥታ፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቻ ተለያዩ 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 16/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል። 

ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሀብታሙ ጉልላት በ34ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪ ሆኗል።

ናትናኤል ዳንኤል በ75ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አቻ አድርጓል። 

ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ17 ነጥብ ስድስተኛ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ12 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዘዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም