የደቡብ እዝ የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የደቡብ እዝ የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እየተከበረ ነው
ባቱ፤ መስከረም 27/2018(ኢዜአ)፡-በአገር መከላከያ ሰራዊት የደቡብ እዝ የ21ኛ ጉና ክፍለ ጦር 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች እና የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት እየተከበረ ነው።
በኦሮሚያ ክልል ባቱ ከተማ እየተከበረ በሚገኘው የምስረታ በዓል ላይ የኢፌዴሪ ጦር ሀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ እና ሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ተገኝተዋል።
በኢትዮጵያ የተጀመሩ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ያለምንም ችግር እንዲከናወን ሰራዊቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ ነው - ሌተናል ጄኔራል መሐመድ ተሰማ
በተጨማሪም የፌዴራል እና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ አባገዳዎችና ሃዳ ሲንቄዎች እንዲሁም የአካባቢው ህብረተሰብ ተገኝቷል።